የአትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት አመራሮች ከኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ጋር ውይይት አደረጉ

ሐምሌ 23/2018፣ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥር የፀረ-አበረታች ቅመሞች ሥራን ከሚመራው የአትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት (AIU) ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ ውይይቶችን አድርጓል።

​በውይይቱ ላይ የአበረታች ቅመሞች ምርመራ ኃላፊ እና የአትሌት ኢንተግሪቲ ዩኒት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቶማስ ካፕዴቬሌ እና ከውድድር ጊዜ ውጪ የሚደረጉ ምርመራዎች ኃላፊ ራፋኤል ሩክስ በባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በአካል ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ጋር በተለያዩ  ጉዳዬች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፣ በተለይም፦ ​ወደ ሙከራ ሥራ ለመግባት ዝግጅት እየተደረገበት ባለው የኤ.ቢ.ፒ (ABP) ምርመራ ላብራቶሪ ሁኔታ፣
​በኢትዮጵያ ያለውን የፀረ-አበረታች ቅመሞች መከላከልና መቆጣጠር እንቅስቃሴ፣
​በቀጣይ በትብብር ሊከናወኑ የታሰቡ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሥራዎችን በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

​በተጨማሪም የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር እና የሥራ ክፍል ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የወቅቱ ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና የ-AIU አመራሮች በጋራ በመሆን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) በመገኘት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ተቋም ጋር በትብብር እየለማ የሚገኘውን የአትሌቶች መረጃ ሥርዓት (Athletes Information System) ያለበትን ደረጃ ገምግመዋል። በግምገማው፦ አጠቃላይ የስርዓቱን ደህንነት፣ ሊያካትታቸው የሚገቡ ጉዳዬችን በተመለከተ እና ተያያዥ ጉዳዬች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *