የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች (Sample Collection Personnel) የስልጠና መርሃ ግብሩ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ጥቅምት 2/2018ዓ.ም
አዳማ
በዛሬው እለት በአበረታች ቅመሞች ውጤት አስተዳደር ሕግ ትግበራና አፈፃፀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአቶ ንጋቱ መኮንን whereabouts mangement ፣ DCO/BCO/Chapeeone professionalism code of conduct ፣ Athletes’s Right and Responsiblity እና Sample collector personnel Right and Responsibility ዙሪያ ሰነድ ቀርቧል እንዲሁም የመረጃ አያያዝ ዲጂታል በሆነ አሰራር በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ሙሉጌታ Introduction to DCO-central ፣ DCO-central practical በገለፃ (Theoretical) እና በተግባር ልምምድ (Practice) ስልጠና ተሰጥቷል ።
ስልጠናው ለ5 ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን ልምድና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች የንድፈ-ኃሳብ ገለፃ እና የተግባር ልምምድ (Practice) የተሰጠ ሲሆን ባለሙያዎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመከወን የሚያስችላቸው የተሻለ እውቀትና ልምድ ለማስያዝ በመቻሉ 42 የዶፒንግ ምርመራ ባለሙያዎች (Sample Collection Personnel) በዛሬው እለት አስመርቋል ።
ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት :- የምርመራ ሥራዎችን በጥራት መስራት እንደሚያስፈልግ እና የአለም አቀፍ አሰራር ስርዓቶችን እና ህጉችን ሙሉ በሙሉ በሚገናኙበት መልኩ የምርመራ ሥራዎች ጥራት ባለውና ሙያዊ የሆነ ሥራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ሙያተኞች የእውቀት ደረጃቸውን እያደገ መሄድ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።
ባለፉት አመታት ተቋሙ ውጤታማ የሆኑ ሥራዎች በመስራቱ በአለም አቀፍ ደረጃም በአህጉር ደረጃ ተጠቃሽ እውቅና የተሰጣቸው ሥራዎች መስራቱን ገልፀዋል ።
አክለውም ተቋሙ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት ሥራዎች የሚሰራ በመሆኑ ሙያተኞችን በዛ ደረጃ በማብቃትና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑ ሙያተኞች ማፍራት እንደሚገባ ገልፀው ሙያተኞችም በዛ ደረጃ እራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል ።
በመጨረሻም ክቡር ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት የምርመራ አሰራር በየጊዜዉ እያደገና ጥራቱ እየጨመረ መሄድ ከተቋሙ የሚጠቀቅ መሆኑን ጠቅሰው ለምርመራ ባለሙያ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በተጠናከረ መንገድ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

