አትሌት ሩቲ አጋ በፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ምክንያት የ6 ዓመት እግድ ተጣለባት
ታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ሩቲ አጋ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ህግን በመተላለፍ አበረታች ቅመም መጠቀሟ በመረጋገጡ እና የተጭበረበረ ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ጥፋተኛ ተብላ የ6 ዓመታት እገዳ ተላልፎባታል።
አትሌቷ እ.ኤ.አ. መጋቢት 15 ቀን 2026 በቻይና በተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ በሰጠችው የሽንት ናሙና “Methylprednisolone” የተባለ የተከለከለ ንጥረ-ነገር መጠቀሟ በምርመራ ተረጋግጧል። ከዚህም ጋር በተያያዘ አትሌቷ መድኃኒቱን በሐኪም ትዕዛዝ እንደወሰደች ለማስረዳት የህክምና ሰነድ አቅርባ የነበረ ቢሆንም፣ በተካሄደው የማጣራት ሥራ ሰነዱ የተጭበረበረ እና ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
በዚህም መሠረት የተከለከለ አበረታች ቅመም ተጠቅማ በመገኘቷ 2 ዓመት እና ሐሰተኛ ሰነድ አቅርቦ ለማጭበርበር በመሞከር 4 ዓመት በአጠቃላይ ከመስከረም 10 ቀን 2026 ጀምሮ ለ6 ዓመታት የሚቆይ ከማንኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እገዳ ተላልፎባታል። በተጨማሪም ከመጋቢት 15 ቀን 2026 ጀምሮ ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች፣ ያሸነፈቻቸው ሜዳሊያዎች፣ ነጥቦች እና የገንዘብ ሽልማቶች ሙሉ በሙሉ ተሰርዘዋል።
********
መስፈንጠሪያውን በመጫን የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይቀላቀሉ፤ ይከታተሉ፤ ይወዳጁ
ቲክቶክ፡- tiktok.com/@eth_ada1
ፌስቡክ፡- facebook.com/ETHNADO
ኤክስ (ቲዊተር)፡- x.com/eadaantidoping
ቴሌግራም፡- t.me/EthiopianADA
ዩቱዩብ፡- youtube.com/@EthiopianAnti-DopingAuthority

