ለኢትዮጵያ ስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎች ማህበር አባላት የፀረ-አበረታች ቅመሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

አዲሰ አበባ፣ መጋቢት 19/2018ዓ.ም.
***

የኢትዮጵያ ስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎች ማህበር 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዬች በውይይት እና በስልጠና በመካሄድ ላይ ይገኛል። ጉባኤው በማህበሩና በኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች  ቅመሞች ባለስልጣን ትብብር የተዘጋጀ ነው።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የማህበሩ የወቅቱ ፕሬዝዳንት አቶ ቢልልኝ መቆያ፣ ባለስልጣን መ/ቤቱ ጉባኤው እንዲካሄድ ላደረገው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበው፣ “የፀረ-አበረታች ቅመሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ዓላማ የስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎች የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅንሰ-ሀሳብን በመረዳት በሙያቸው የተሻለ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ታስቦ ነው።” ብለዋል።

ስልጠናው የፀረ-አበረታች ቅመሞች መሠረታዊ ጉዳዬችና አተገባበር በሚል ርዕስ በባለስልጣን መ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ የአበረታች ቅመሞች ጽንሰ-ሀሳብ፣ የህግ ጥሰት ዓይነቶችንና የሚያስከትሉትን ቅጣት፣ የአበረታች ቅመሞች የተፅዕኖ አድማስን በተመለከተ እና የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ በኢትዬጵያ ለምን አስፈለገ በሚሉ እና ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ተሰጥቷል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ከተሳታፊዎች አጠቃላይ በስልጠናው በቀረቡ ጉዳዬች ዙሪያ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *