በደራርቱ ቱሉ የስፖርት ስልጠናና ምርምር ኢንስቲትዩት ስር ታቅፈው የሚገኙ አሰልጣኞች፣ አትሌቶች እና ለድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በፀረ-አበረታች ቅመሞች/ ዶፒንግ/ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም
ሱሉልታ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በሱሉልታ ከተማ ደራርቱ ቱሉ የስፖርት ስልጠናና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከስሩ ታቅፈው የሚገኙት ለከፍተኛ አመራሮች፣ አሰልጣኞች እና አትሌቶች እና ለድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በፀረ- አበረታች ቅመሞች / ዶፒንግ/ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ።
ስልጠናውን የአበረታች ቅመሞች መከላከል ግንዛቤ እና ህዝብ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ወይንሸት ሙሉጌታ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የአሠራር ስርዓቶች እንዲሁም በምርመራና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ገለጻና ማብራሪያ ተደርጓል።
በቀረበው ገለጻ እና ስልጠና ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

