የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሞያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

መስከረም   28/2018 ዓ.ም
አዳማ

የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች ( Sample Collection Personnel’s Training) ከአትሌት ኢንተግሪቲ ዩኒት ጋር በጋራ በመቀናጀት በአዳማ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል  ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሀገራችን በየደረጃው የአበረታች  ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራ ለማካሄድ በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር  400/2009 ስልጣንና ሀላፊነት ተሰቶጥቷል። በዚሁም መሠረት የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች በበጎ ፈቃደኝነት ለሀገራቸው እና ለህዝባችሁ የዜግነት ሃላፊነትን አስተዋፅኦ ለሚያበረክቱ  ሙያተኞች የእውቀት ደረጃቸውን በማሳደግና የምርመራ ሥራዎች የአለም አቀፉን የአሰራር ስርዓት በመከተል ተግባራዊ  ለማድረግ ያለመ ስልጠና ነው  ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል በስልጠና መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት:-
አበረታች ቅመሞች ጉዳይ የሀገራችን ስፖርት ተግዳሮት እየሆነ መምጣቱና ከአገራችን ባለፈ በአለም አቀፍ ደረጃ ስፖርቱን እየፈተነ ያለ የስፖርቱ ተደማሪ ችግር እየሆነ መምጣቱ አቶ መኮንን ይደርሳል ተናግሯል።
አቶ መኮንን አክለውም ዶፒንግ የስፖርቱን ተአማኒነት በማሳጣት ስፖርተኞች ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችሉበት መስመር እያስወጣ ስፖርተኞች ተፈጥሯዊ ባልሆነ መንገድ አበረታች ቅመሞች በመጠቀም ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ውድድሮችን እያሸነፉ እንዳለ ገልፀዋል ።
አበረታች ቅመም ወይም ዶፒንግ ከስፖርቱ ውጪም በዜጎች ላይ የጤና ችግር እየሆነ መምጣቱ ባለፈ ማህበራዊ ችግር እያስከተለና የሀገራችን ገፅታ እያበላሽ እንደሚገኝ ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል ተናግሯል።
አክለውም ተቋሙ ከተቋቋመ ጀምሮ ሰፋፊ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልፀው የምርመራ ቁጥጥር ስራዎች የመዘርጋት የማጠናከር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑና የምርመራ ስርአቱ በሀገራችን በተሟላ መንገድ ወደ ተግባር እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።
የምርመራ አቅማችንን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ እና የሙያተኛም ቁጥር በማሳደግ የምርመራ ባለሙያዎች በማሰልጠንና የምርመራ አቅምን የበለጠ በማጎልበትና የባለሙያ ቁጥሩና ጥራቱንም የበለጠ ለማሳደግ አላማ ያደረገ ነው ።
በሀገራችን አትሌት ባይሎጂካል ላብራቶሪ ለሟቋቋም ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በቅንጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑና የቅድመ እውቅና በማግኘት በ2018 በሙከራ ደረጃ ምርመራ ስራ እንደሚጀመር ክቡር ዳይሬክተሬቱ ጠቁሟል ።
ስልጠናው በዋናነት  የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ ብቃት ያላቸው ሙያተኞችን ለማፍራት አለም አቀፍ ሙያተኞችና የባለስልጣኑ ባለሙያዎች በቅንጅት  በዛሬው ዕለትም በተለያዪ ርዕሰ ጉዳዩች በገለፃና በonline ሙያዊ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *