የባለስልጣን መስሪያቤት የሥራ እንቅስቃሴዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደረጉ መምጣታቸው ተገለፀ
መጋቢት 30፣ 2018 ዓ.ም
አዲስአበባ
**
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ9ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ3 ዓመት የመካከለኛ ዘመን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ውይይት ከሰራተኞች ጋር አካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት እና ውይይቱን የመሩት የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል፣ መድረኩ የአፈፃፀም ክፍተቶች እና ጥንካሬዎች የሚለዩበት፤ ጉድለቶችን የምናርምበት እና ጥንካሬዎችን አጉልተን የምናወጣበት መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም የዕቅድ አፈፃፀሙ በሁሉም መስክ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እያሳዩ መምጣታቸው የተረጋገጠበት እንደሆነ ገልፀዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በአገር ውስጥ ምንም ዓይነት መነሻ የሚሆን ተሞክሮ ባልነበረበት የማይገመቱ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀው፣ ባለስልጣን መስሪያቤቱ በአሁኑ ወቅት ውጤታማ ከሚባሉ ውስን ተቋማት መካከል ስሙ የሚጠራበት ደረጃ እንደሚገኝ አሳውቀው ወጤቱ ሁሉም ሠራተኛ የየድርሻውን በሃላፊነት በመወጣቱ የተገኘ እንደሆነ ተናግረዋል።
መድረኩ በወ/ሮ ስርጉት በየነ የስትራቴጂክ ጉዳዬች ሥራ-አስፈፃሚ የ9ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ3 ዓመት የመካከለኛ ዘመን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ተጠናቋል።

