የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) በ2018 በጀት ዓመት በነበረው የስራ አፈፃፀምና ባስመዘገባቸው በርካታ ስኬቶች የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
የባህልና ስፖርት ሴክተር የ2018 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤ ክልሎች/የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ከሐምሌ 29/2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ተቋማት በመለየት የዕውቅና ሽልማት አበርክቷል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በነበረው የእቅድ አፈፃፀም ውጤታመነትና በተለያዩ መለኪያዎች ባስመዘገበው ስኬት ልዩ ተሸላሚ ሊሆን ችሏል። በመሆኑም ባለስልጣን መ/ቤቱ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ጉዳይ እና ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከሆኑት ክብርት ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ እንዲሁም ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ተቀብሏል።
ተቋሙ በአለም አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ምዘናዎችም ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ሲሆን በቀጣይም እነዚህ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል።

