የኢትዮጵያ  ፀረ -አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር ሲካሄድ የቆየ የስልጠናና የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ

ሰኔ 24/2018ዓ.ም
አዳማ

የኢትዮጵያ  ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ስፖርቱን ንፅህናና ፍትሃዊነት የመጠበቅ ተልዕኮ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የስፖርት ልማትንና ጥራትን የማስፋፋት፣ የስፖርተኞችን ደህንነት የመጠበቅና የስፖርት ማህበረሰቡን የማንቃት ስራዎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው። ይህንን የጋራ ተልዕኮ በውጤታማነት ለመወጣት እና በዘርፉ ያለውን ፍትሃዊነትን የማረጋገጥ፣ የማስፈጸም እንዲሁም ግንዛቤን ለማሳደግ አቅም ለማጠናከር  ከፌዴራል ፣ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ አመራሮች እና  ከባለድርሻ አካላት ጋር ከሰኔ 23-24 ዓ.ም በአዳማ ከተማ  የስልጠናና የውይይት አካሄዷል ።

በመድረኩ ላይ በባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የአበረታች ቅመሞች መከላከል፣ ግንዛቤ እና የህዝብ ንቅናቄ መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአቶ ፈለቀ ዋለልኝ አማካኝነት፤ የአበረታች ቅመሞች  መሠረታዊ ጉዳዮች እንዲሁም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአበረታች ቅመሞች ውጤት አስተዳደር ሕግ ትግበራና አፈፃፀም መሪ ስራ አስፈፃሚ  በአቶ ንጋቱ መኮንን በአበረታች ቅመሞች ህግ አተገባበር  እንዲሁም የ2018 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በወ/ሮ ስርጉት በየነ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ-አስፈፃሚ ቀርበው ሰፊ ውይይት  ተካሂዶባቸዋል።

ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት አመት በፀረ-አበረታች ቅመሞች የስራ እንቅስቃሴዎች  ያከናወናቸው ተግባራቶችን ሪፖርት በማቅረብ እንዲሁም ለሌሎች ክልሎች በፀረ- አበረታች የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ አሰራሮች ላይ በመድረኩ አቅርበዋል፡፡

በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ  ቡድን መሪ አቶ አዛናው መኳንንት የ2ኛው በመካከለኛው ዘመን እቅድና የ2019 በጀት አመት እቅድ የቀረበ ሲሆን በመድረኩ ክልሎች ባቀረቡት ሪፖርት እና  አጠቃላይ በመድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየት ቀርቧ።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ  ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ  መድረኩን ሲያጠቃልሉ በቀረበው ጥያቄና አስተያየት  ምላሽና ማብራሪያ  በመስጠት በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው ጉዳዮች አቅጣጫ አስቀምጠዋል፦

የስፖርት ፖሊሲው ንፁህ ስፖርትን ልዩ ትኩረት የተሰጠው ስለሆነ የፀረ-አበረታች ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ስለሆነ የድርሻችን በመውሰድ መተግበር ይኖርብናል ፣

የስፖርት  አመራሮች  በዶፒንግ ጉዳይ  ያለውን እውቀትና አረዳድ  ወሳኝ መሆኑ በመረዳት ግንዛቤዎችን  ቀጣይነት ባለው  ደረጃ የበለጠ ማሳደግና ማጎልበት ይኖርባችኋል ፣

በቀረቡ ተሞክሮዎች ላይ ተቋማት አንዱ  ከሌላኛው  የወሰደውን ተሞክሮ መነሳሳትና ቁጭት ሊፈጥር እንደሚገባ በማሳሰብ  በቀጣይ የተቀራረበ  አፈፃፀም  እንዲኖር  ተግታችው መስራት  የምችሉበት እድል የፈጠረ ስለሆነ በቀጣይ የተሞክሮ ልውውጥ  ተግባራዊ  እንደምታደርጉት እምነት አለኝ በማለት ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ መድረኩን አጠቃሏል ።

በመድረኩ  ከፌዴራል፣ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ከትምህርት ስልጠና የስራ ክፍል ሀላፊዎች፣ከዕቅድ ዝግጅት የስራ ክፍል ሀላፊዎች እና ከዶፒንግ ተጠሪ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *