“አበረታች ቅመሞችን ለመቆጣጠር የመድኃኒት መደብሮችና የፈርማሲ ባለሙያዎች ሙያዊ ኃላፊነትና ገዴታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል” አቶ መኮንን ይደርሳል
አበረታች ቅመም (ዶፒንግ) በስፖርቱና በሀገር ገጽታ ላይ የሚያስከትለውን ውስብስብ ችግር በመረዳት የመድኃኒት ክትትልና ቁጥጥር እና የመድኃኒት መደብር ተቋማት እንዲሁም የፈርማሲ ባለሙያዎች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበት የኢትዮጰያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ አበረታች ቅመሞችን ቁጥጥርና ክትትልን በተመለከተ ከኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አመራሮችና ባለሙያዎች እና ከመድኃኒት መደብር ባለቤቶችና ባለሙያዎች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጰያ ፀረ-አበረታች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል፣ አበረታች ቅመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተለያዩ ጊዜያት ከመድሃኒት መደብሮች ባለቤቶችና ባለሙያዎች ጋር የተለያየ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ሲካሄዱ መቆየታቱን ገልፀዋል። ከዚህም ባለፈ የአበረታች ቅመሞች ጉዳይ አሳሳቢና በሀገርም ላይም የሚፈጥረው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ማህበረሰቡም ላይ ሰፊ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመንግስት በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት የህግ ጥሰት ፈፀመው በሚገኘ አትሌቶች እና ሌሎች አካላት ላይ ተጠያቂ የማድረግ እና የተለያየ አስተማሪ ቅጣቶችን የማስተላለፍ ስራዎች እየተከናወኑ ቢገኝም አሁንም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ርብርብን የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑን አመላክተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፡- በሀገርና በግለሰቦች ላይ የጤና፣ የስነ-ልቦና፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ አልፎም የሀገርን ክብር የሚያጎድፍ ተግባር በመሆኑ የሁሉንም አካላት ተሳትፎ የሚሻ ጉዳይ እንደሆነ እና በተለይ ደግሞ በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብሩ እንደቀጠለ የሚገኝ ሲሆን፣ በስፖርት የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን በሚመለከት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፋርማኮሎጂ የት/ት ክፍል ኃላፊ በሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሰለሞን አሠፋ በንድፈ-ሀሳብ የተደገፈ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
#EthAdaCampaign
መስፈንጠሪያውን በመጫን የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይቀላቀሉ፤ ይከታተሉ፤ ይወዳጁ
ቲክቶክ፡- tiktok.com/@eth_ada1
ፌስቡክ፡- facebook.com/ETHNADO
ኤክስ (ቲዊተር)፡- x.com/eadaantidoping
ቴሌግራም፡- t.me/EthiopianADA
ድረ-ገፅ፡- ethada.org.et





